ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት እና መረጃ

ክህሎት ያለው ዜጋ፣ የተረጋጋ የሥራ ዕድል እና ዘላቂ ምርታማነት!

የሥራና ክህሎት ቢሮ ወቅታዊ መረጃዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አቅጣጫዎችን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ መመሪያዎችን፣ አዋጆችን እና የምዘና/ስልጠና ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ያቀርባል።

4+

ወቅታዊ ዜናዎችና ቪዲዮዎች

0+

ለህዝብ ክፍት የሆኑ መመሪያዎችና ቅጾች

5

ዋና ዳይሬክቶሬቶችና የሥራ ክፍሎች

ወቅታዊ ዜናዎች፣ ምስሎች እና ቪዲዮዎች

የቢሮው ዋና ዋና ክንውኖች፣ ስልጠናዎች እና ይፋዊ መግለጫዎች

ቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን በዲጂታል ቴክኖሎጂ …
📅 Nov 06, 2026 ✍️ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ (Poster)

ቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን በዲጂታል ቴክኖሎጂ …

ቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማዘመን ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት ወሳኝ ነው የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን በዲጂታል ቴክኖሎጂና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዘ ማድረግ የሥልጠና ጥራትን ለማሳደግና ከሥራ ዓለም ፍላጎት ጋር የተጣጣመ የሰው ኃይል ለማፍራት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር በዲጂታል ቴክኖሎጂና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የታገዘ የሥልጠና ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የፌዴራልና የክልል የስልጠና ባለሙያዎች፣ ለኮሌጅ ዲኖች፣ ለአሰልጣኝ መምህራን የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ አዝመራ ከበደ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂን ከሥልጠና ሥርዓቱ ጋር ማቀናጀት የትምህርት አሰጣጡን ዘመናዊና አካታች ከማድረጉም በላይ የአሰልጣኞችንና የሰልጣኞችን አቅም ለማሳደግ እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል። እንደ አቶ አዝመራ ገለጻ፣ በሥልጠና ሥርዓቱ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀም ተወዳዳሪና ብቁ ሰልጣኞች ከማፍራት ቀለል ያሉ ማሰላሰል በሚያስችሉ ጨዋታዎች ላይ የተመሠረቱ የማስተማሪያ ዘዴዎችንና ማስመሰያዎችን(simulations) መጠቀም የሰልጣኞችን ተሳትፎ በማሳደግ በቀላሉ እውቀትን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ያግዛል። ቅይጥ ትምህርት (Blended Learning) አተገባበርም የፊት ለፊት ትምህርትን ከዲጂታል ትምህርት ጋር በማቀናጀት የመማር ሂደቱን የሚያቀላጥፍና የሥልጠና ጥራትን የሚያሳድግ አሰራር መሆኑ ተጠቁመል። በዚህ ረገድ፣ ለክልል ቢሮዎች፣ ለሲኦሲ ማዕከላትና ከ70 በላይ ለሚሆኑ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የዲጂታል መሠረተ ልማት መሟላቱንና ከ500 በላይ መምህራን በአዳዲስ የማስተማር ዘዴዎች ላይ ሥልጠና ማግኘታቸውን አቶ አዝመራ ገልጸዋል። አያይዘውም፣ የዲጂታል ሥልጠና ሥርዓቱ ውጤታማ እንዲሆን የክልል ቢሮዎች፣ የኮሌጅ አመራሮችና አሰልጣኞች የባለቤትነት ሚናቸውን በመወጣት የተጀመሩ ሥራዎችን በቀጣይነት መከታተልና ማስፋፋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሠራተኞችን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ …
📅 Nov 06, 2026 ✍️ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ (Poster)

የሠራተኞችን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ …

የሠራተኞችን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ የኮንፌዴሬሽኑ ሚና ወሳኝ ነው — ክብርት ሰላማዊት ዳዊት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ኮንፌዴሬሽኑ ባለፉት ዓመታት የሠራተኞችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ሥራዎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ክብርት ሰላማዊት ዳዊት በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኮንፌዴሬሽኑ የሠራተኞችን መብትና ተጠቃሚነትን በማስጠበቅ፣ የሠራተኛና የአሠሪ ግንኙነትን በማጠናከር እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሰላምን በማስፈን ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ሚኒስቴሩ በዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት ኮንፌዴሬሽኑን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እንደሚሠራም አመልክተዋል። በውይይቱ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ካሳሁን ፎሎን ጨምሮ የኮንፌዴሬሽኑ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የሥራ ዕድል ፈጠራ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት …
📅 Nov 06, 2026 ✍️ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ (Poster)

የሥራ ዕድል ፈጠራ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት …

የሥራ ዕድል ፈጠራ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት የልማት አጋሮች ጠንካራ ትብብር ወሳኝ ነው። ክቡር አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የልማት አጋር ድርጅቶች የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተያዙ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ድጋፋቸውን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ገለጹ። ሚኒስትር ዴኤታው ከአውሮፓ ሕብረት ልዑክ እና ከጀርመን የልማት ትብብር (GIZ) ተወካዮች ጋር በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ወደፊት በትኩረት ተጠናክረው መቀጠል በሚገባቸው የትብብር መስኮች ላይ አተኩረው ተወያይተዋል። ክቡር አምባሳደር የልማት አጋሮች በዘርፉ እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው፣ በተለይም የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በሚቀይሩ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ላይ የጋራ ጥረትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ የሥራ ዕድሎችን ለዜጎች ለመፍጠር የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የልማት አጋሮች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመው የሚፈጠረው የሥራ ዕድል በቁጥር የሚለካ ብቻ ሳይሆን ዜጎች ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው፣ ኢኮኖሚያዊ ነፃነታቸውን እንዲያጎለብቱና የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያስችል መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። የGIZ ተወካዮች በበኩላቸው በኢኮኖሚ ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎትና ትምህርት ልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በስደተኞች ማኅበራዊ ተሳትፎ ዙሪያ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማጠናከር ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎትን ለማሻሻል …
📅 Nov 06, 2026 ✍️ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ (Poster)

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎትን ለማሻሻል …

የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ለማሻሻልና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ ክቡር አቶ አወሉ አብዲ – የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክቡር አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ። ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ከሚኒስቴሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ላይ በተስተዋሉ ችግሮች፣ መንስኤዎቻቸውና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ ነው። በውይይቱ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ችግሮች፣ መንስኤዎቻቸውንና የመፍትሔ አማራጮችን የሚያብራራ ሰነድ ቀርቦ ዝርዝር ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ለሀገር ትልቅ ሀብት መሆኑን ጠቁመው ሥርዓቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካትም ትልቅ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል። በሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በጥልቀት መለየትና በቅድሚያ መፍትሔ የሚያስፈልጋቸውን ችግሮች መለየት እንደሚገባም ገልጸዋል። ችግሮቹ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በተዘጋጀ አቅጣጫ መፍትሔ እንዲያገኙ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። ከቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር፣ ከሰው ኃይልና አደረጃጀት፣ እንዲሁም ከሕግና አሠራር ጋር የተያያዙ ችግሮች በአስቸኳይ ተለይተው እንዲቀርቡም አሳስበዋል። እነዚህን ችግሮች በየደረጃው በመፍታት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ችግሮቹ እስኪፈቱ ድረስ አገልግሎቶች መቋረጥ የለበትም ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ክፍተቶቹን እየፈቱ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ አብራርተዋል። በውይይቱ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ መካከለኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የህዝብ ሰነዶች፣ አዋጆች፣ መመሪያዎች እና ቅጾች

ያለ ምንም ምዝገባ በቀጥታ የሚወርዱ ይፋዊ የቢሮው ሰነዶች

በዚህ መስፈርት የተገኘ የህዝብ ሰነድ የለም።